Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

doc

Department of Corrections
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about DC Department of Corrections services for Amharic speakers.

የኤጀንሲ ስም፥ የዲሲ ማረሚያ ቤቶች መምሪያ

የተልዕኮ መግለጫ ቃል፥
የዲሲ ማረሚያ ቤቶች (D.C. Department of Corrections /DCDOC) ተልዕኮ ሥርዓት ያለው፣ ደሕንነቱ አስተማማኝ፣ በደንብ የተጠበቀ እና ሰብዓዊነትን
የተላበሰ ድባብን ፍርድ እስኪሰጣቸው የታሰሩ እና የተፈረደባቸው እስረኞችን ማቆያ ቦታን በማቅረብ፣ እነዚሁ ታራሚዎችን ወደ ማኅበረሰቡ መልሰው
ውጤታማ በሆኑ መልኩ እንዲቀላቀሉ በማዘጋጀት ለዲስትሪክቱ ነዋሪ ዜጎች ሕዝባዊ የደሕንነት ዋስትና መስጠት ነው። የ DCDOC ድርጅታዊ ሥርዓት
በዋኝነት በሁለት የማረሚያ ተቋማት የተገነባ ነው—እነዚህም የዲሲ እስር ቤት በመባል የሚታወቀው የማዕከላዊ እስር ቤት ተቋም እና በግል ድርጅት
የሚተዳደረው የማረሚያ ቤት ተቋም ናቸው። በተጨማሪ፣ DCDOC ከአራት በግል የሚተዳደሩ ወንድ/ሴት ታራሚዎችን የሚያስተናግዱ እስረኞች
ከማህበረሰቡ ጋር ከመቀላቀላቸው በፊት የሚቆዩባቸው ድርጅቶች ጋር አብሮ የመስራት ውል አለው። በነዚህ ተቋማት ውስጥ እንዲገቡ የተደረጉ አጥፊዎች
ፍርድ የሚጠባበቁ፣ የተፈረደባቸው አነስተኛ ወንጀለኞች፣ የተፈረደባቸው ከባድ ወንጀለኞች እና ቃላቸውን ሰጥተው እንዲፈቱ የሚጠባበቁ እስረኞችን
ያካትታሉ።
አንኳር መርሃ ግብሮች፥
DCDOC ማረሚያ ተቋማት በቀን ሃያ አራት ሰዓታት፣ በዓመት 365 ቀናት ይሠራሉ። እያንዳንዱ ማረሚያ ተቋም የቪዲዮ ጉብኝት፣ የክስ አስተዳደር፣
የሪኮርዶች ሥራ ክንውን ማስኬድ፣ የምግብ ዝግጅት፣ ሃይማኖታዊ ዝግጅት፣ የልብስ እጥበት፣ የቤተ መጻሕፍት ግብዓቶችን መጠቀም፣ የታራሚ አቤቱታ
ማስተናገድ እና ሕጋዊ ጉብኝትን ጨምሮ፣የታራሚ የግል ባሕሪ ማረቂያ እና የድጋፍ አገልግሎቶችን ይሰጣል። የአሜሪካ ማረሚያ ቤቶች ማኅበር (American
Correctional Association /ACA) እና ብሔራዊ የማረሚያ ቤቶች ጤና እንክብካቤ (National Commission on Correctional Health Care
/NCCHC) ዕውቅና የሰጡዋቸው ሁሉን አቀፍ የጤና እና የሥነአእምሮ አገልግሎቾች በተጨማሪ በኮንትራት በተቀጠረ የሕክምና አገልግሎት አቅራቢ ይሰጣሉ።
ከዚህ በተጨማሪ፣ እያንዳንዱ ተቋም ለታራሚዎች ወደ ማኅበረሰቡ በተሳካ ሁኔታ መልሰው እንዲቀላቀሉ የሚያግዙ አገልግሎቶችን ይሰጣል። የንጥረ ነገሮች
አላግባብ መጠቀም (አደንዛዥ ዕጽ) ማስወገጃ ሕክምና፣ መልሶ መግቢያ ፕሮግራሚንግ፣ ተቋማዊ የሥራ ዝርዝሮች፣ የቀለም ትምህርት አገልግሎቶችን
የጎልማሶች መሰረተ ትምህርት፣ GED መሰናዶ እና ልዩ ትምህርት በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (District of Columbia Public
Schools /DCPS) በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶችን ያካትታሉ።
አገልግሎቶች፥
የቪዲዮ ጎብኝት
በዲሲ እስር ቤት የሚደረጉ ሁሉም ማኅበራዊ ጉብኝቶች በመምሪያው በዲሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ሕንፃ (ከማረሚያ ቤቱ አጠገብ የሚገኘው) አዲሱ የቪዲዮ
ጎብኝት ማዕከል ውስጥ ይከናወናሉ። ጉብኝቶች ለማድረግ ቀጠሮ ለማስያዝ በበይነመረብ (ድረገጽ) https://visitation.doc.dc.gov/app በኩል ወይም በስልክ
ቁጥር 1 (888) 906-6394 ወይም (202) 442-7270 (ከማክሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 9 amእስከ ቀኑ 5 pm ድረስ) በመደወል ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል።
ጉብኝቶች የሚደረጉት በየሳምንቱ ከረቡዕ ጀምሮ እስከ እሁድ ባሉት ቀናት እኩለ ቀን ጀምሮ እስከ ምሽቱ 8 pm ድረስ ነው። የመጀመሪያው ጉብኝት ክፍለ ጊዜ
እኩለ ቀን ላይ ሲጀምር የመጨረሻው ክፍለ ጊዜ ደግሞ ከምሽቱ 7 pm ላይ ይጀምራል። ሕጋዊ ጉብኝቶች በአካል የሚደረጉ ጉብኝቶች ሆነው በቀን ሃያአራት
ሰዓት ሳምንቱን ሙሉ (24/7) ሊደረጉ ይቻላሉ። በኮምፒዩተር የተደገፈ የታራሚ ተቀማጭ ገንዘብ
ሁሉም ታራሚዎች በሚወሰዱበት ሂደት ወቅት የፋይናንስ መለያ ሒሳብ ይቀናበርላቸዋል። ይህ የመለያ ሒሳብ ሁሉንም በእጃቸው የሚገኝ ገንዘብ፣
ከማናቸውም የሥራ ዝርዝሮች የተገኘ ገቢ፣ ከቤተሰብ አባላት እና ጓደኞች የሚሰጣቸውን ገንዘብ ይይዛል። ገንዘብ ወደ DCDOC ታራሚ በዌስተርን ዩኒየን
(Western Union)፣ OffenderConnect፣ ወይም በቪዲዮ ጎብኝት ማዕከሉ ያለውን የታራሚ ኮኔክተር ኪዮስክ (Inmate Connector Kiosk) በመጠቀም
መላክ ይቻላል። ተቀማጭ የሆነ ገንዘብ ታራሚ ለሚጠቀማቸው የስልክ አገልግሎቶች፣ ከምግብ ቤት የሚያደርጋቸው ግዢዎች ወይም ከውጭ ላሉ ግለሰቦች
ወይም ተቋማት የሚከፍለው ክፍያ መክፈያ ሊሆን ይችላል።
የወንጀል ሰለባ መረጃ እና ማሳወቂያ በየቀኑ
DCDOC የወንጀል ሰላባ መረጃ እና ማሳወቂያ በየቀኑ (Victim Information and Notification Everyday (VINE) ሥርዓትን ያስተዳድራል። VINE
በኮምፒዩተር የተደገፈ የወንጀል ሰለባ ማሳወቂያ ሥርዓት ሲሆን ለወንጀል ሰለባዎች የወንጀል ፈጻሚው ታራሚ ኹናቴ ሲቀየር ማለትም ከእስር ሲለቀቅ፣
ከማረሚያ ቤት ወደ ሌላ ሲዛወር፣ በፍርድ ቤት ቀጠሮ ሲቀርብ፣ ሲያመልጥ ወይም እንደገና ሲታሰር እንዲያውቁት ያደርጋል። የ VINE ምዝገባ ለማድረግ
በስልክ ቁጥር 1-877-329-7894 ወይም በበይነመረብ መስመር ላይ በቀጥታ በ www.vinelink.com አድራሻ መጠቀም ይቻላል።
የትርጉም አገልግሎቶች
ከተለያዩ በ DCDOC ውስጥ ያሉ ቢሮዎች በራስዎ ቋንቋ እገዛ ለማግኘት፣ እባክዎ የእኛን ዋናው መሥሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 202-673-7316 ያነጋግሩ።
ስለጉብኝቱ ሥራ አፈጻጸም ሂደት የሚነሱ ጥያቄዎች በስልክ ቁጥር 202-442-7270 ወይም 1-888-906-6394 ከማክሰኞ እስከ እሁድ ከጠዋቱ 9:00 am
እስከ ቀኑ 5:00 pm ድረስ ይስተናገዳሉ። ወደ እኛ ቢሮዎች ሲደውሉ፣ እርስዎን ለማገዝ አንድ ሠራተኛ በእርግጠኝነት ሁሌም ከሚገኝ አስተርጓሚ ጋር
እንዲገናኙ ያደርግዎታል።
መገኛ አድራሻ መረጃ፥
DC Department of Corrections
3924 Minnesota Avenue, NE
2nd Floor
Washington, DC 20019
ስልክ ቁጥር፥ (202) 698-4932
ፋክስ፥: (202) 671-2043
ኢሜይል፥ [email protected]